YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 92

92
1በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
2 # መዝ. 33፥1፤ 147፥1። ጌታን ማመስገን መልካም ነው፥
ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፥
3በማለዳ ምሕረትን፥
በሌሊትም እውነትህን ማውራት
4 # መዝ. 33፥2፤ 144፥9። ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥
ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
5አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፥
በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና።
6 # መዝ. 131፥1፤ 139፥6፤17፤ ጥበ. 13፥1፤ 17፥1። አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው!
ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
7የማያስተውል ሰው አያውቅም።
አላዋቂ አይረዳውም።
8 # መዝ. 37፥35። ኃጢአተኞች እንደ ሣር ቢበቅሉ
ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ቢለመልሙ፥
ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው።
9አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፥
10 # መዝ. 68፥1-2፤ 125፥5። አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥
ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
11 # መዝ. 23፥5፤ መዝ. 75፥11፤ ዘዳ. 33፥17። እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ#92፥11 ዕብራይስጡ “እንደ ጐሽ ቀንድ ቀንዴን ከፍ ከፍ አደረግህ ይላል።”
በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
12 # መዝ. 91፥8። ዓይኔም ጠላቶቼን ቃኘች፥
ጆሮዬም በእኔ ላይ የተነሡትን ክፉዎች ሰማች።
13 # መዝ. 1፥3፤ 52፥10፤ ኤር. 17፥8። ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
14በጌታ ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
15ያንጊዜ ገና በሽምግልናም ያፈራሉ
ገና ወተታማና አርንጓዴ ሆነው ይኖራሉ።
16 # ዘዳ. 32፥4። ጌታ ትክክለኛ እንደሆነ ይነግራሉ፥
ዓለቴ ነው፤ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝሙረ ዳዊት 92