YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 81

81
1ለመዘምራን አለቃ፥ በዋሽንት፥ የአሳፍ መዝሙር።
2 # መዝ. 43፥4፤ 68፥26፤ 149፥3፤ 150፥3-4፤ ዮዲ. 16፥1። ለኃይላችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ፥
ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
3ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥
ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፥
4 # ዘሌ. 23፥24፤ ዘኍ. 29፥1። በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን
መለከትን ንፉ፥
5 # ዘፀ. 23፥14። ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥
የያዕቆብም አምላክ ፍርድ።
6ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አድርጎ አቆመው።
ያላወቅሁትን ቋንቋ ሰማሁ።
7 # ዘፀ. 1፥14፤ 6፥6። ጫንቃውን ከሸክም፥
እጆቹንም በቅርጫት#81፥7 ጡብ የሚሸከሙበት ቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።
8 # መዝ. 95፥8፤ ዘፀ. 2፥23፤ 17፥7፤ 19፥16፤ ዘኍ. 20፥13፤ 27፥14። በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥
ከተሰወረ የሞገድ ስፍራ መለስሁልህ፥
በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ።
9ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነግርሃለሁም፥
እስራኤል ሆይ፥ ምነው በሰማኸኝ!
10 # ዘፀ. 20፥2-6፤ ዘዳ. 5፥6-10። አንተስ ብትሰማኝ ሌላ አምላክ አይሆንልህም፥
ለሌላ አምላክም አትሰግድም።
11ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ
እኔ ጌታ አምላክህ ነኝና፥
አፍህን አስፋ እሞላዋለሁም።
12ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥
እስራኤልም አላዳመጠኝም።
13 # ኤር. 3፥17፤ 7፥24። እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥
በልባቸውም አሳብ ሄዱ።
14 # ኢሳ. 48፥18። ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥
እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፥
15 # ዘሌ. 26፥7-8። ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥
በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፥
16የጌታ ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥
ዘመናቸውም ለዘለዓለም በሆነ ነበር፥
17 # መዝ. 147፥14፤ ዘዳ. 32፥13-14። ከስንዴም ስብ ባበላኋቸው ነበር፥
ከዓለቱም ማር ባጠገብኋቸው ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝሙረ ዳዊት 81