መዝሙረ ዳዊት 77
77
1ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።
2በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥
ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።
3 #
መዝ. 50፥15፤ 88፥2። በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት፥
እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥
ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም።
4 #
ዮናስ 2፥8። እግዚአብሔርን ሳስታውስ እተክዛለሁ#77፥4 ግሪኩ “እደሰታለሁ” ይላል።፥
ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች።
5ዐይኖቼ እንዲተጉ ያዝሃቸው፥
ስለተረበሽኩ አልተናገርሁም።
6የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥
የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥
7 #
መዝ. 143፥5፤ ዘዳ. 32፥7። በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥
ነፍሴንም አነቃቃኋት።
8 #
መዝ. 13፥2፤ 44፥24፤ 74፥1፤ 80፥5፤ 89፥47፤ ሰቆ.ኤ. 3፥31። ጌታ ለዘለዓለም ይጥላልን?
እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን?
9ለዘለዓለምስ ርኅራኄው ተቈረጠችን?
የሰጠውስ ቃል ኪዳን ለዘመናት አልቆአልን?
10እግዚአብሔርስ ማዘኑን ረሳን?
በቁጣውስ ርኅራኄውን ዘጋውን?
11 #
መዝ. 17፥7፤ 18፥36፤ ዘፀ. 15፥6፤12። ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥
የልዑል ቀኝ መለወጡ።
12 #
መዝ. 143፥5። የጌታን ሥራ አስታወስሁ፥
የቀደመውን ተኣምራትህን አስታወሳለሁና፥
13በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥
ሥራህንም አሰላስላለሁ።
14 #
መዝ. 18፥31፤ ዘፀ. 15፥11። አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፥
እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
15 #
መዝ. 86፥10፤ 89፥6። ተኣምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ።
ለሕዝብህ ኃይልህን አስታወቅሃቸው።
16 #
ዘፍ. 46፥26-27፤ ነህ. 1፥10። የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥
ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።
17 #
መዝ. 18፥16፤ 114፥3፤ ናሆም 1፥4። አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥
ውኆችም አይተውህ ፈሩ፥
ጥልቆችም ተነዋወጡ።
18 #
መዝ. 18፥14-15፤ 29፤ 144፥6፤ ኢዮብ 37፥3-4፤ ጥበ. 5፥21፤ ዕን. 3፥10-11፤ ዘካ. 9፥14። ደመኖች ውሃን አዘነቡ፥ ደመኖች ድምፅን ሰጡ፥
ፍላጾችህም በየአቅጣጫው ወጡ።
19 #
መዝ. 18፥8፤ 97፥4፤ 99፥1፤ ዘፀ. 19፥16፤ መሳ. 5፥4-5። የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነበረ፥
መብረቆች ለዓለም አበሩ፥
ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም።
20 #
ነህ. 9፥11፤ ጥበ. 14፥3፤ ኢሳ. 51፥10፤ ዕን. 3፥15። መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥
ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤
ዱካህ ግን አልታወቀም።
21 #
መዝ. 78፥52፤ ኢሳ. 63፥11-14፤ ሆሴዕ 12፥14፤ ሚክ. 6፥4። በሙሴና በአሮን እጅ
ሕዝብህን እንደ በጎች መራሃቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 77: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

:
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in