YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 70

70
1ለመዘምራን አለቃ፥ ለመታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 40፥14-18። አቤቱ፥ አድነኝ፥
አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።#መዝ. 71፥12።
3 # መዝ. 35፥4፤26። ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጐስቁሉም፥
ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም።
4 # መዝ. 35፥21፤25። እሰይ እሰይ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
5 # መዝ. 35፥27። የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥
ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
6እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ አቤቱ፥ እርዳኝ፥
ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ፥ አትዘግይ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 70