YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 54

54
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት። 2#1ሳሙ. 23፥19፤ 26፥1።ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ፥
3አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥
በኃይልህም ፍረድልኝ።
4አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥
የአፌንም ቃል አድምጥ፥
5 # መዝ. 86፥14። እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥
ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና።
እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።
6 # መዝ. 118፥7። እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥
ጌታም ለሕይወቴ ደጋፊ ነው።
7 # መዝ. 143፥12። ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥
በእውነትህም አጥፋቸው።
8በፈቃዴ እሠዋልሃለሁ፥
አቤቱ፥ መልካም ነውና ስምህን አመሰግናለሁ፥
9 # መዝ. 59፥11፤ 91፥8፤ 92፥12። ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥
ዓይኔም የጠላቶቼን ውድቀት አይታለችና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 54