YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 52

52
1ለመዘምራን አለቃ የዳዊት ትምህርት። 2#1ሳሙ. 21፥8፤ 22፥6።ኤዶማዊው ዶይቅ መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል ብሎ በነገረው ጊዜ፥
3ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኩራራለህ?
ሁልጊዜስ በመተላለፍ?
4 # መዝ. 12፥3፤ 59፥8፤ 120፥2-3፤ ሲራ. 51፥3። አንደበትህ ጥፋትን ያስባል፥
እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
5 # ኤር. 4፥22፤ ዮሐ. 3፥19-20። ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥
ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ።
6 # ኤር. 9፥4። የሚያጠፋ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ።
7 # መዝ. 27፥13፤ 28፥5፤ 56፥14፤ ኢዮብ 18፥14፤ ምሳ. 2፥22፤ ኢሳ. 38፥11። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፥
ከድንኳንም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥
ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
8 # መዝ. 44፥14፤ 64፥9። ጻድቃን አይተው ይፈራሉ፥
በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦
9 # ኢዮብ 31፥24፤ ምሳ. 11፥28። እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥
በሀብቱም ብዛት የታመነ፥
በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።
10 # መዝ. 1፥3፤ 92፥12-14፤ ኤር. 11፥16፤ 17፥8። እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፥
ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ርኅራኄ ታመንሁ።
11 # መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 149፥1። አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥
በቅዱሳንህም ዘንድ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 52