YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 29

29
1ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ።
ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
2 # መዝ. 68፥35፤ 96፥7-9። የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥
በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ።
3የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥
አምላክ በብዙ ውኆች ላይ።
4 # መዝ. 46፥7፤ 77፥18-19፤ ኢዮብ 37፥4፤ ኢሳ. 30፥30። የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥
የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው።
5የጌታ ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፥
ጌታ የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6እንደ ጥጃ ሊባኖስን#29፥6 የሊባኖስን ተራራዎች
እንደ ጎሽ ጥጃ ስርዮንን#29፥6 የሔርሞን ተራራ ያዘልላቸዋል።
7የጌታ ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8የጌታ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥
ጌታ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥
ጫካዎቹንም ይገልጣል፥
ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10 # ባሮክ 3፥3። ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥
ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11 # መዝ. 68፥36። ጌታ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፥
ጌታ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 29