YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 15

15
1የዳዊት መዝሙር።
# ኢሳ. 56፥7። አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2 # መዝ. 119፥1። በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥
በልቡም እውነትን የሚናገር።
3በአንደበቱ የማይሸነግል፥
በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥
የሚቀርቡትን የማይሰድብ።
4ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥
ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥
ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።
5 # ዘፀ. 22፥24፤ 23፥8። ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥
በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል።
እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in