YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 149

149
1 # መዝ. 22፥23፤ 26፥12፤ 35፥18፤ 40፥10፤ ዮዲ. 16፥1። ሃሌ ሉያ።
ለጌታ አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፥
ውዳሴው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።
2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥
የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ።
3 # መዝ. 68፥26፤ 81፥2-3፤ 87፥7፤ 150፥3-4። ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፥
በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።
4ጌታ በሕዝቡ ተደስቶአልና፥
የዋሃንንም በማዳኑ ያስጌጣቸዋል።
5ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፥
በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
6 # ነህ. 4፥10-12፤ 2መቃ. 15፥27። የእግዚአብሔር ምስጋና በጉሮሮአቸው ነው፥
ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥
7 # ጥበ. 3፥8። በአሕዛብ ላይ በቀልን፥
በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፥
8ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥
አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፥
9የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ።
ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት።
ሃሌ ሉያ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝሙረ ዳዊት 149