ትንቢተ ሐጌ መግቢያ
መግቢያ
በትንቢተ ሐጌ የተጠናቀሩት አጫጭር መልእክቶች እግዚአብሔር ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ምእተ ዓመት፥ በነቢዩ ሐጌ አማካይነት ያስተላለፋቸው ናቸው። ሕዝቡ ከስደት ተመልሰው በኢየሩሳሌም መኖር ከጀመሩ ጥቂት ዓመቶች ያለፋቸው ቢሆንም እንኳን ቤተ መቅደሱ ገና እንደ ፈረሰ ነበር፤ ስለዚህ መልእክቱ የሕዝቡ መሪዎች ቤተ መቅደሱን እንዲያድሱ የሚገፋፋ ነበር፤ ሕዝቡ በእውነተኛ ፀፀት ንሥሐ ከገቡ፥ እግዚአብሔር ወደ ፊት ሰላምና ብልጽግና እንደሚሰጣቸው ይናገራል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ጌታ ቤተ መቅደሱ እንዲሠራ ማዘዙ (1፥1-15)
2. ጌታ ለሕዝቡ የሰጠው የበረከትና የማጽናናት ተስፋ (2፥1-23)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ትንቢተ ሐጌ መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in