YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ሶፎንያስ መግቢያ

መግቢያ
ነቢዩ ሶፎንያስ መልእክቱን ያስተላለፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባተኛው ምእት ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ሲሆን፥ ምናልባትም ያ ጊዜ ንጉሥ ኢዮስያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በስድስት መቶ ኻያ አንድ ዓመት የቃል ኪዳን ተሐድሶ ከማድረጉ ዐሥር ዓመት ቀደም ብሎ ሳይሆን አይቀርም። መጽሐፉ ሌሎች ነቢያት የተናገሩትን ትንቢት የያዘ ነው፤ እነርሱም ይሁዳ ለባዕዳን አማልክት በመስገዷ ምክንያት ቅጣት በሚደርስባት ጊዜ ጥፋትና መደምሰስ እንደሚደርስባት የሚያመለክቱ ናቸው፤ እንዲሁም እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ሌሎችንም ሕዝቦች እንደሚቀጣ ይገልጣል። በኢየሩሳሌም ላይ የመፍረስ አደጋ ቢደርስባትም ከጊዜ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ትመለሳለች፤ ትሑታንና ጽድቅን የሚከተሉ ሕዝብም ይኖሩባታል።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
1. በይሁዳ ላይ የሚተላለፍ ፍርድ 1፥1-18
2. ንስሓ መግባት 2፥1-3
3. በእስራኤል ጐረቤቶች የሚተላለፍ ፍርድ 2፥4-15
4. ይሁዳና ሌሎች ወገኖች ወደ ጌታ መመለሳቸው 3፥1-20

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in