YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ዘካርያስ መግቢያ

መግቢያ
የነቢዩ የዘካርያስ መጽሐፍ በሁለት ክፍሎች የተመደበ ነው፤
1. ም. 1-8 ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአምስት መቶ ኻያ እስከ አምስት መቶ ዐሥራ ስምንት ዓመት ባሉት ዓመቶች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ነቢዩ ዘካርያስ የተናገራቸውን የትንቢት ቃላት የያዘ ክፍል ነው፤ እነዚህም የትንቢት ቃላት በራእይ መልክ የቀረቡ ሲሆን ስለ ኢየሩሳሌም መታደስ፥ ስለ ቤተ መቅደሱ እንደገና መሠራት፥ ስለ እግዚአብሔር ሕዝብ መንጻትና ወደፊት ስለሚመጣው የመሲሑ ዘመን የሚናገሩ ናቸው።
2. ም. 9-14 ያለው ክፍል ዘግየት ብለው የተነገሩትን የትንቢት ቃላት የያዘ ነው፤ እነዚህም የትንቢት ቃላት የሚናገሩት ወደፊት ስለሚመጣው መሲሕና ስለ መጨረሻው ፍርድ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. የመጀመሪያ ራእይ፥ ፈረሶችና ፈረሰኞች (1፥1-17)
2. ሁለተኛ ራእይ የእንስሳ ቀንዶች (1፥18-21)
3. ሦስተኛ ራእይ፥ ስለ መለኪያ ገመድ (2፥1-13)
4. አራተኛ ራእይ፥ ነቢዩ ዘካርያስ ስለ ሊቀ ካህናቱ ያየው (3፥1-10)
5. አምስተኛ ራእይ፥ የመቅረዝና የወይራ ዛፎች (4፥1-14)
6. ስድስተኛ ራእይ፥ በራሪው የመጽሐፍ ጥቅል (5፥1-4)
7. ሰባተኛ ራእይ፥ በቅርጫት ውስጥ ያለች ሴት (5፥5-11)
8. ስምንተኛ ራእይ፥ አራት ሠረገሎች (6፥1 -8)
9. ኢያሱን ቀብቶ ለማንገሥ የተሰጠ ትእዛዝ (6፥9-15)
10. እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነውን ጾም የማይቀበል መሆኑ (7፥1-7)
11. አለመታዘዝ የስደት ምክንያት መሆኑ (7፥8-14)
12. እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም የሰጠው ተስፋ (8፥1-23)
13. እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚአድንና ጠላቶቻቸውን እንደሚቀጣ (9፥1—11፥3)
14. ሁለቱ የእስራኤል መሪዎች (11፥4-17)
15. የኢየሩሳሌም ድል አድራጊነት (12፥1-9)
16. ሕዝቡ በጦር ለተወጋው ማዘኑና ወደ ጌታ መመለሱ (12፥10—13፥9)
17. የመጨረሻ ጦርነትና የጌታ ድል (14፥1-21)

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in