YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 87

87
ስለ ኢየሩሳሌም የቀረበ ውዳሴ
1እግዚአብሔር ከተማውን
በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ።
2እግዚአብሔር ከእስራኤል መኖሪያዎች ሁሉ ይልቅ
የጽዮንን ደጆች ይወዳል።
3አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ!
አስደናቂ ነገሮች ስለ አንቺ ተነግረዋል።
4ለእኔ በመታዘዝ የሚያገለግሉኝን ሕዝቦች
በምመዘግብበት ጊዜ ግብጽንና ባቢሎንን እጨምራለሁ፤
ከኢየሩሳሌም ተወላጆች ጋር የፍልስጥኤምን፥
የጢሮስንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች እጨምራለሁ።
5ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት
ስለ ጽዮን፦ “ይህም ሕዝብ፥ ያም ሕዝብ በእርስዋ ውስጥ
ተወልደዋል” ይባላል።
6እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሁሉ ይመዘግባል፤
እያንዳንዱንም “በጽዮን የተወለደ” ብሎ ይጠራዋል።
7ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “የበረከታችን ሁሉ መገኛ ጽዮን ናት”
እያሉ በደስታ ይዘምራሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መጽሐፈ መዝሙር 87