YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 57

57
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ!
ራራልኝ፤ ማረኝ፤
ለደኅንነቴ አንተ ዘንድ እሸሸጋለሁ፤
አደጋው እስኪያልፍ ድረስ
በጥበቃህ ሥር እከለላለሁ።
2የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ
ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጣራለሁ።
3እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤
የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና
ታማኝነቱን ይገልጣል።
4ጥርሶቻቸው እንደ ጦሮችና ቀስቶች፥
ምላሶቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች በሆኑ፥
ሰውን በሚበሉ አንበሶች መካከል ተደፍቼ ተኝቼአለሁ።
5አምላክ ሆይ!
ከሰማያት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።
6ጠላቶቼ እኔን ለመያዝ ወጥመድ ዘርግተውብኛል፤
ሁለንተናዬን የሚያጐብጥ ተስፋ መቊረጥ ደረሰብኝ፤
በመንገዴ ጒድጓድ ቈፈሩ፤
ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ወደቁበት።
7ልቤ ጽኑ ነው፤ አምላክ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤
በመልካም ቃና እዘምርልሃለሁ!
8ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤
በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ!
እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
9እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤
በአሕዛብም መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
10ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤
ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
11አምላክ ሆይ! ከሰማያት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም ከምድር ሁሉ በላይ ይሁን። #1ሳሙ. 22፥1፤ 24፥3።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in