YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 133

133
ስለ ወንድማማችነት ፍቅር የቀረበ ውዳሴ
1ወንድማማች አብረው ይኖሩ ዘንድ
ምንኛ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው!
2በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥
እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥
መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው።
3ከሔርሞን ተራራ ወደ ጽዮን ኰረብቶች
እንደሚንጠባጠብ ጤዛ ነው፤
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የሆነውን
ሕይወትና በረከት የሚሰጠው በዚያ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in