YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 113

113
የእግዚአብሔርን ቸርነት የሚገልጥ ምስጋና
1እግዚአብሔር ይመስገን!
እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች
የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ!
2አሁንም ለዘለዓለም ስሙ ይመስገን።
3ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ
የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!
4እግዚአብሔር የመንግሥታት ሁሉ ገዢ ነው፤
ክብሩም ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው።
5እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፤
ዙፋኑም ከሁሉ በላይ ነው።
6ነገር ግን ሰማይንና ምድርን
ወደ ታች ይመለከታል።
7ድኾችን ከትቢያ
ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል።
8የልዑላን ጓደኞች ያደርጋቸዋል፤
ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያስቀምጣቸዋል።
9መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤
ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል።
እግዚአብሔር ይመስገን!

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in