YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ናሆም መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ናሆም ከጥንት ጀምሮ የእስራኤል ቀንደኛ ጠላት ስለ ነበረችው የአሦር ዋና ከተማ ስለ ነነዌ መደምሰስ የሚያበሥር ቅኔ ነው። ነነዌ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባተኛው ምእት ዓመት መጨረሻ ላይ መደምሰስዋ፥ እግዚአብሔር በጨካኝና በትዕቢተኛ ሕዝብ ላይ እንዴት እንደሚፈርድ ያሳያል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. አስፈሪው የእግዚአብሔር ቊጣ 1፥1-6
2. በአሦር ላይ የተላለፈው ፍርድ ለእስራኤል ሕዝብ ተስፋ ማስገኘቱ 1፥7-15
3. የአሦር ዋና ከተማ ነነዌ መጥፋት 2፥1—3፥19

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in