YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መሳፍንት መግቢያ

መግቢያ
መጽሐፈ መሳፍንት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ከገቡበት ጊዜ አንሥቶ ንጉሣዊው መንግሥት እስከ ተመሠረተበት ጊዜ ድረስ፥ ያለውን ታሪክ የያዘ ነው፤ ይህም ዘመን የእስራኤል ሕዝብ ጣዖትን በማምለክ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅን ያበዙበት ጊዜ ነበር። ይህም ታሪክ የሚያመለክተው “መሳፍንት” የተባሉት ጀግኖች የፈጸሙአቸውን ተግባሮች ነው፤ ከእነዚህም መሳፍንት መካከል አብዛኞቹ የጦር መሪዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም በጣም የታወቀው የጀግንነት ሥራው ከምዕራፍ 13-16 ተዘርዝሮ የሚገኘው ሶምሶን የተባለው ሰው ነው።
ከመጽሐፉ የምናገኘው ታላቅ ትምህርት የእስራኤል ሕዝብ ህልውና የሚረጋገጠው ለእግዚአብሔር ባላቸው ታማኝነት ሲሆን፥ ለእርሱ ታማኞች ሳይሆኑ ሲቀሩ ዘወትር ጥፋት ይደርስባቸው እንደ ነበር የሚያስገነዝበው ነው፤ ከዚህም የበለጠ ሌላ ነገር አለ፤ ይኸውም ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ያለውን ታማኝነት በማጓደሉ ጥፋት ቢደርስበትም እንኳ፥ ንስሓ ገብቶ ወደ እርሱ በተመለሰ ቊጥር እግዚአብሔር ያድነው ነበር።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሀ. እስከ ኢያሱ ሞት ድረስ የነበረው ሁናቴ 1፥1—2፥10
ለ. የእስራኤል መሳፍንት 2፥11—16፥31
ሐ. የተለያዩ ድርጊቶች 17፥1—21፥25

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in