YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ዕንባቆም መግቢያ

መግቢያ
የመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች በዕንባቆምና በእግዚአብሔር መካከል የተደረጉ ንግግሮች ናቸው፤ ዕንባቆም በይሁዳ ፍትሕ መጓደልና የወንጀል ተግባር ላይ ተቃውሞውን አሰማ፤ እግዚአብሔርም ባቢሎናውያን የይሁዳን ሕዝብ ይቀጣሉ ብሎ መልስ ሰጠው፤ ከዚህ በኋላ ግን ዕንባቆም ባቢሎናውያን ከይሁዳ ሕዝብ የበለጠ ኃጢአተኞች ስለ ሆኑ እንዴት የይሁዳ ሕዝብ በነርሱ እጅ ይቀጣል? ብሎ ጌታን ጠየቀ፤ ጌታ ለዕንባቆም ጥያቄ፥ ባቢሎናውያንም በተራቸው ወደፊት ይቀጣሉ ብሎ መልስ ሰጠ።
የመጨረሻው ምዕራፍ ዕንባቆም ስለ ጌታ ክብርና ሥልጣን ምስጋና ያቀረበበት ጸሎት ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. የዕንባቆም ስሞታና የጌታ መልስ 1፥1—2፥4
2. በኃጢአተኞች ላይ የተላለፈ ፍርድ 2፥5-20
3. የዕንባቆም ጸሎት 3፥1-19

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in