YouVersion Logo
Search Icon

ማቴዎስ 1:1-16

ማቴዎስ 1:1-16 NASV

የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ከረዓብ ወለደ፤ ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ኢዮሆራምን ወለደ፤ ኢዮሆራም ዖዝያንን ወለደ፤ ዖዝያን ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤ አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞንን ወለደ፤ አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፣ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤ አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄም አዛርን ወለደ፤ አዛር ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የማርያም ዕጮኛ ነበር።

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy