YouVersion Logo
Search Icon

ኢሳይያስ 4

4
1በዚያ ቀን ሰባት ሴቶች
አንዱን ወንድ ይዘው፣
“የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤
የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤
በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣
ውርደታችንን አስቀርልን!” ይሉታል።
እግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ
2በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል። 3በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋራ ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። 4ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ#4፥4 ወይም በእግዚአብሔር መንፈስ ማለት ነው። ያነጻታል። 5ከዚያም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤ 6ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፣ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል።

Currently Selected:

ኢሳይያስ 4: NASV

Highlight

Copy

Compare

Share

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in