1
ትንቢተ ኤርምያስ 44:16-17
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም። ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፥ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፥ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 44:16-17
2
ትንቢተ ኤርምያስ 44:18
ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርስዋም የመጠጥን ቍርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፥ እኛ በሁሉ ነገር ተቸግረናል፥ በሰይፍና በራብ አልቀናል።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 44:18
3
ትንቢተ ኤርምያስ 44:23
ስላጠናችሁ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ስለ በደላችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 44:23
Home
Bible
Plans
Videos