1
መጽሐፈ መሳፍንት 6:12
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጦ፦ አንተ ጽኑዕ ኃያል ሰው፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው።
Compare
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:12
2
መጽሐፈ መሳፍንት 6:14
እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፦ በዚህ በጉልበትህ ሂድ፥ እስራኤልንም ከምድያም እጅ አድን፥ እነሆ፥ ልኬሃለሁ አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:14
3
መጽሐፈ መሳፍንት 6:16
እግዚአብሔርም፦ በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:16
4
መጽሐፈ መሳፍንት 6:13
ጌዴዎንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ? ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፥ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:13
5
መጽሐፈ መሳፍንት 6:15
እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው፥ እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:15
6
መጽሐፈ መሳፍንት 6:11
የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው በአድባሩ ዛፍ በታች ተቀመጠ፥ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጠመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:11
7
መጽሐፈ መሳፍንት 6:24
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም፦ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለአቢዔዝራውያን በምትሆነው በዖፍራ አለ።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:24
8
መጽሐፈ መሳፍንት 6:17
እርሱም፦ በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ፥ የምትናገረኝም አንተ እንደ ሆንህ ምልክት አሳየኝ፥
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:17
9
መጽሐፈ መሳፍንት 6:23
እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን፥ አትፍራ፥ አትሞትም አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:23
10
መጽሐፈ መሳፍንት 6:1
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 6:1
Home
Bible
Plans
Videos