1
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
Compare
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
2
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢያት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
3
ኦሪት ዘጸአት 20:12
አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:12
4
ኦሪት ዘጸአት 20:8
የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:8
5
ኦሪት ዘጸአት 20:7
የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:7
6
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
7
ኦሪት ዘጸአት 20:17
የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:17
8
ኦሪት ዘጸአት 20:16
በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:16
9
ኦሪት ዘጸአት 20:14
አታመንዝር።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:14
10
ኦሪት ዘጸአት 20:13
አትግደል።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:13
11
ኦሪት ዘጸአት 20:15
አትስረቅ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 20:15
Home
Bible
Plans
Videos