1
ኦሪት ዘጸአት 2:24-25
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፤ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ።
Compare
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:24-25
2
ኦሪት ዘጸአት 2:23
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:23
3
ኦሪት ዘጸአት 2:10
ሕፃኑም አደገ፤ ወደ ፈርዖንም ልጅ ዘንድ አመጣችው፤ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። “እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና” ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው።
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:10
4
ኦሪት ዘጸአት 2:9
የፈርዖንም ልጅ፦ “ይህን ሕፃን ወስደሽ አጥቢልኝ፤ ዋጋሽንም እሰጥሻለሁ፤” አለቻት። ሴቲቱም ሕፃኑን ወስዳ አጠባችው።
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:9
5
ኦሪት ዘጸአት 2:5
የፈርዖንም ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፤ ደንገጥሩዋንም ልካ አስመጣችው።
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:5
6
ኦሪት ዘጸአት 2:11-12
በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፤ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው የወንድሞቹን የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ። ወዲህና ወዲያም ተመለከተ፤ ማንንም አላየም፤ ግብፃዊውንም ገደለ፤ በአሸዋም ውስጥ ሸሸገው።
Explore ኦሪት ዘጸአት 2:11-12
Home
Bible
Plans
Videos