1
መጽሐፈ መክብብ 4:9-10
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፥ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።
Compare
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:9-10
2
መጽሐፈ መክብብ 4:12
አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:12
3
መጽሐፈ መክብብ 4:11
ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፥ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል?
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:11
4
መጽሐፈ መክብብ 4:6
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል።
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:6
5
መጽሐፈ መክብብ 4:4
ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራውም ዘንድ ቅንዓት እንዲያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:4
6
መጽሐፈ መክብብ 4:13
ድሀና ጠቢብ ብላቴና ተግሣጽን መቀበል ከእንግዲህ ወዲህ ከማያውቅ ከሰነፍ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል።
Explore መጽሐፈ መክብብ 4:13
Home
Bible
Plans
Videos