1
መጽሐፈ መክብብ 11:9
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዓይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።
Compare
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:9
2
መጽሐፈ መክብብ 11:10
ሕፃንነትና ጕብዝና ከንቱዎች ናቸውና ከልብህ ኀዘንን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉን ነገር አስወግድ።
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:10
3
መጽሐፈ መክብብ 11:4
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም።
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:4
4
መጽሐፈ መክብብ 11:5
የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም።
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:5
5
መጽሐፈ መክብብ 11:6
ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:6
6
መጽሐፈ መክብብ 11:2
ለሰባት ደግሞም ለስምንት እድል ፈንታን ክፈል፥ በምድር ላይ የሚሆነውን ክፉ ነገር ምን እንደሆነ አታውቅምና።
Explore መጽሐፈ መክብብ 11:2
Home
Bible
Plans
Videos