1
የሐዋርያት ሥራ 5:29
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
Compare
Explore የሐዋርያት ሥራ 5:29
2
የሐዋርያት ሥራ 5:42
ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
Explore የሐዋርያት ሥራ 5:42
3
የሐዋርያት ሥራ 5:3-5
ጴጥሮስም፦ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ? ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም” አለው። ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።
Explore የሐዋርያት ሥራ 5:3-5
4
የሐዋርያት ሥራ 5:38-39
አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።”
Explore የሐዋርያት ሥራ 5:38-39
Home
Bible
Plans
Videos