1
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:20-21
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እግዚአብሔር ያናገረለትንም ተስፋ ይቀራል ብሎ አልተጠራጠረም፤ በእምነት ጸና እንጂ፤ ለእግዚአብሔርም ክብርን ሰጠ። እግዚአብሔርም የሰጠውን ተስፋ ሊያደርግለት እንደሚችል በፍጹም ልቡ አመነ።
Compare
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:20-21
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17
“ለብዙዎች አሕዛብ አባት አደርግሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታንን በሚያስነሣቸው፥ የሌሉትንም እንደ አሉ በሚያደርጋቸው በአመነበት በእግዚአብሔር ፊት አብርሃም የሁላችን አባት ነው።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:24-25
ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለውን፥ ሊያስነሣንና ሊያጸድቀን የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ በአስነሣው ስለምናምን ስለ እናም ነው እንጂ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:24-25
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:18
አብርሃም “ዘርህ እንዲሁ ይሆናል” ብሎ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባልነበረ ጊዜ የብዙዎች አሕዛብ አባት እንደሚሆን አመነ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:18
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:16
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:16
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:7-8
“መተላለፋቸው የቀረላቸው፥ ኀጢአታቸውም የተሰረየላቸው ብፁዓን ናቸው። እግዚአብሔርም በደሉን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።”
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:7-8
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 4:3
መጽሐፍስ ምን ይላል? አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 4:3
Home
Bible
Plans
Videos