1
ትንቢተ ኤርምያስ 17:7-8
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
በእግዚአብሔር የሚታመን፥ ተስፋውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 17:7-8
2
ትንቢተ ኤርምያስ 17:9
“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 17:9
3
ትንቢተ ኤርምያስ 17:10
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 17:10
4
ትንቢተ ኤርምያስ 17:5-6
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በሰው የሚታመን የሥጋ ክንዱንም በእርሱ የሚያስደግፍ፥ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚርቅ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንደ አለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይኖርበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 17:5-6
5
ትንቢተ ኤርምያስ 17:14
አቤቱ! ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤ አንተ መመኪያዬ ነህና።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 17:14
Home
Bible
Plans
Videos