1
መጽሐፈ መሳፍንት 7:2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።
Compare
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 7:2
2
መጽሐፈ መሳፍንት 7:7
ጌታም ጌዴዎንን፥ “ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ በጠጡት ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችሃለሁ፤ የቀሩት በሙሉ ወደየመጡበት ይመለሱ” አለው።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 7:7
3
መጽሐፈ መሳፍንት 7:3
አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ ዐሥርም ሺህ ቀሩ።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 7:3
4
መጽሐፈ መሳፍንት 7:4
ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “አሁንም ሰዎቹ ብዙ ናቸው፤ ወደ ወንዝ ይዘሃቸው ውረድ፤ በዚያም እጸልይልሃለሁ። ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን፥ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሂድ’ የምለው፥ ከአንተ ጋር አይሄድም።”
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 7:4
5
መጽሐፈ መሳፍንት 7:5-6
ስለዚህ ጌዴዎን ሰዎቹን ወደ ወንዝ ይዞአቸው ወረደ፤ እዚያም ጌታ፥ “ውሻ በምላሱ እየጨለፈ እንደሚጠጣ ሁሉ፥ በምላሳቸው የሚጠጡትን፥ በጉልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። ሦስት መቶ ሰዎች ውሃውን በእጃቸው እያፈሱ ጠጡ፤ የቀሩት ሁሉ ግን ለመጠጣት በጉልበታቸው ተንበረከኩ።
Explore መጽሐፈ መሳፍንት 7:5-6
Home
Bible
Plans
Videos