1
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:8
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል ጌታ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:8
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:9
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:9
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:6
ጌታ በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:6
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:7
ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ ጌታም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:7
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:1
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:1
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:10-11
ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ እንድታበቅልና እንድታፈራም እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ፥ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥ ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል፤ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:10-11
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:12
እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልል ይላሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:12
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:3
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 55:3
Home
Bible
Plans
Videos