1
ኦሪት ዘዳግም 8:18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:18
2
ኦሪት ዘዳግም 8:3
ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:3
3
ኦሪት ዘዳግም 8:2
ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:2
4
ኦሪት ዘዳግም 8:17
በልብህም፦ ‘ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ’ እንዳትል፥ አስብ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:17
5
ኦሪት ዘዳግም 8:11
“ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:11
6
ኦሪት ዘዳግም 8:5
እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:5
7
ኦሪት ዘዳግም 8:10
ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ፥ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር ጌታን አምላክህን ትባርካለህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:10
8
ኦሪት ዘዳግም 8:6
እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የጌታ የአምላክህን ትእዛዞች ጠብቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:6
9
ኦሪት ዘዳግም 8:16
በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:16
10
ኦሪት ዘዳግም 8:12-14
በልተህ በምትጠግብበት፥ መልካምም ቤት ሠርተህ በምትኖርበት ጊዜ፥ የከብቶችህና የበጎችህ መንጋ፥ ብርህና ወርቅህም፥ እንዲሁም ያለህ ሁሉ በበዛልህ ጊዜ፥ ልብህ እንዳይታበይና፥ ከግብጽም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ ጌታን አምላክህን እንዳትረሳ፤
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:12-14
11
ኦሪት ዘዳግም 8:7-9
ጌታ አምላክህ ወደ መልካም ምድር፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች፥ ምንጮችም ወዳሉባት ምድር፥ የስንዴና ገብስ፥ የወይንና በለስ ዛፍ እንዲሁም ሮማን፥ የወይራ ዛፍና ማር ወደ ሞሉባት ምድር፥ ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያስገባሃል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:7-9
12
ኦሪት ዘዳግም 8:1
“በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ ጌታም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት፥ ዛሬ እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዝ ሁሉ ለማድረግ ተጠንቀቁ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:1
13
ኦሪት ዘዳግም 8:4
በእነዚህ አርባ ዓመታት የለበስኸው ልብስ አላረጀም፥ እግርህም አላበጠም።
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:4
14
ኦሪት ዘዳግም 8:15
መርዘኛ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከዓለት ድንጋይም ውኃን ያፈለቀልህን፥
Explore ኦሪት ዘዳግም 8:15
Home
Bible
Plans
Videos