1
ኦሪት ዘዳግም 5:16
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:16
2
ኦሪት ዘዳግም 5:33
በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ጌታ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:33
3
ኦሪት ዘዳግም 5:9-10
በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም። ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን አደርጋለሁ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:9-10
4
ኦሪት ዘዳግም 5:8
“ ‘በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፥
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:8
5
ኦሪት ዘዳግም 5:7
“ ‘ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:7
6
ኦሪት ዘዳግም 5:11
“ ‘የጌታን የአምላክህ ስም በከንቱ አትጥራ፥ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አይቀርምና።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:11
7
ኦሪት ዘዳግም 5:29
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:29
8
ኦሪት ዘዳግም 5:12
“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ እንድትቀድሰው፥ የሰንበትን ቀን ጠብቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:12
9
ኦሪት ዘዳግም 5:21
“ ‘የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፥ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም አገልጋዩንና አገልጋይቱን፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ንብረት ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።’
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:21
10
ኦሪት ዘዳግም 5:18
“ ‘አታመንዝር።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:18
11
ኦሪት ዘዳግም 5:20
“ ‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:20
12
ኦሪት ዘዳግም 5:17
“ ‘አትግደል።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:17
13
ኦሪት ዘዳግም 5:19
“ ‘አትስረቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:19
14
ኦሪት ዘዳግም 5:15
አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፥ ጌታ እግዚአብሔር በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:15
15
ኦሪት ዘዳግም 5:13-14
ስድስት ቀን ሥራ፥ ሥራህንም ሁሉ አከናውን፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:13-14
16
ኦሪት ዘዳግም 5:6
“ ‘ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 5:6
Home
Bible
Plans
Videos