1
ወደ ሮም ሰዎች 2:3-4
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አንተ ሰው! እንዲህ በሚያደርጉት ሰዎች ላይ እየፈረድክ፥ እነርሱ የሚያደርጉትን ስታደርግ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን? ወይስ የእግዚአብሔርን የደግነቱንና የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ብዛት ትንቃለህን? እግዚአብሔር ደግነቱን ያበዛልህ አንተን ወደ ንስሓ ለመምራት እንደ ሆነ አታውቅምን?
Compare
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:3-4
2
ወደ ሮም ሰዎች 2:1
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 2:11
እግዚአብሔር በሰዎች መካከል አያዳላም።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:11
4
ወደ ሮም ሰዎች 2:13
በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁ ሕጉን ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው እንጂ ሕጉን ሰምተው በሥራ ላይ የማያውሉት አይደሉም።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:13
5
ወደ ሮም ሰዎች 2:6
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደየሥራው ይሰጠዋል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:6
6
ወደ ሮም ሰዎች 2:8
የራሳቸውን ጥቅም በሚፈልጉ፥ ለእውነት በማይታዘዙና ለዐመፅ በሚታዘዙ ዐድመኞች ላይ ግን የእግዚአብሔር ቊጣና መቅሠፍት ይመጣባቸዋል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:8
7
ወደ ሮም ሰዎች 2:5
እንግዲህ አንተ ንስሓ ባለመግባትህና እልኸኛ በመሆንህ የእግዚአብሔር ቊጣና ትክክለኛ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን ቅጣትህ እንዲበዛ ታደርጋለህ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 2:5
Home
Bible
Plans
Videos