1
ትንቢተ ኤርምያስ 6:16
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 6:16
2
ትንቢተ ኤርምያስ 6:14
የሕዝቤንም የስብራት ቊስል እንደ ቡጭራት በመቊጠር በሚገባ አያክሙትም፤ እንዲሁም ሰላም ሳይኖር ‘ሰላም ነው፤ ሰላም ነው፤’ ይላሉ።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 6:14
3
ትንቢተ ኤርምያስ 6:19
ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 6:19
4
ትንቢተ ኤርምያስ 6:10
እኔም መልሼ እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ብነግራቸውና ባስጠነቅቃቸው ማን ሊሰማኝ ይችላል? እነርሱ እልኸኞች ስለ ሆኑ፥ ቃልህን መስማት አይፈልጉም፤ የአንተን ቃል ስነግራቸው በንቀት መሳቂያ ያደርጉኛል።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 6:10
Home
Bible
Plans
Videos