1
ትንቢተ ኤርምያስ 4:1-2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥ በእውነትና በቅንነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ ብትምሉ ሕዝቦች ይባረካሉ፤ በዚህም ይመካሉ።”
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 4:1-2
2
ትንቢተ ኤርምያስ 4:22
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 4:22
3
ትንቢተ ኤርምያስ 4:18
ይሁዳ ሆይ! ይህ ሁሉ የደረሰብሽ በአካሄድሽና በክፉ ሥራሽ ምክንያት ነው፤ ይህም ሁሉ የመረረ መከራ የመጣብሽ በኃጢአትሽ ምክንያት ስለ ሆነ ወደ ሰውነትሽ ዘልቆ ልብሽን አቊስሎታል።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 4:18
Home
Bible
Plans
Videos