1
ትንቢተ ኢሳይያስ 62:4
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 62:4
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 62:6-7
ኢየሩሳሌም ሆይ! በቅጥሮችሽ ላይ ቀንና ሌሊት ዝም የማይሉ ጠባቂዎችን አኑሬአለሁ፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምትለምኑ ዕረፍት አታድርጉ። ኢየሩሳሌምን እስኪመሠርታትና በምድር ሁሉ ዝነኛ ከተማ እስከሚያደርጋት ድረስ ሳታቋርጡ አሳስቡት።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 62:6-7
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 62:3
አንቺ በእግዚአብሔር እጅ እንዳለው የተዋበ አክሊልና በአምላክሽም እጅ እንዳለው የነገሥታት ዘውድ ትሆኚአለሽ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 62:3
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 62:5
ጐልማሳ ድንግሊቱን ሙሽራ አድርጎ እንደሚወስድ፥ የፈጠረሽ እግዚአብሔርም ለአንቺ እንደ ባል ይሆንልሻል፤ ወንዱም ሙሽራ በሴትዋ ሙሽራ ደስ እንደሚሰኝ፥ እግዚአብሔርም በአንቺ ደስ ይለዋል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 62:5
Home
Bible
Plans
Videos