1
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:17
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:10
ተራራዎችና ኰረብቶች ሊናወጡና ሊፈርሱ ይችላሉ፤ እኔ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የሰላምንም የተስፋ ቃሌን ለዘለዓለም እጠብቅልሻለሁ፤” ይላል ለአንቺ የሚራራ እግዚአብሔር።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:10
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4
ኀፍረትም ሆነ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ በወጣትነትሽ ጊዜ የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺአለሽ፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ብቸኛ ሆነሽ ያሳለፍሽውን የስድብ ዘመን አታስታውሺም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:4
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5
ይህም የሚሆነው ፈጣሪሽ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ባልሽ ስለሚሆንና ‘የምድር ሁሉ አምላክ’ ተብሎ የሚጠራው የእስራኤል ቅዱስ አዳኝሽ ስለ ሆነ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:2
የምትኖሪበትን የድንኳንሽንም ቦታ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽም እንዲዘረጉ አድርጊ፤ አታጥብቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስማዎችሽንም አጠንክሪ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:2
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:13
“ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም የተሟላ ይሆናል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:13
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:8
እጅግ ከመቈጣቴ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሬ እራራልሻለሁ፤ ይላል አዳኝሽ እግዚአብሔር።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:8
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:7
ለጥቂት ጊዜ ብቻ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በታላቅ ርኅራኄ እመልስሻለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:7
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:9
“በኖኅ ዘመን ‘ምድርን በውሃ መጥለቅለቅ እንደገና አላጠፋትም’ ብዬ ቃል እንደ ገባሁ እነሆ አሁንም ‘በአንቺ ላይ እንደገና አልቈጣም’ ብዬ ቃል እገባልሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ተግሣጽ አላደርስብሽም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:9
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 54:12
የግንቦችሽን ጒልላት በቀይ መረግድ፥ የቅጽር በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቊ፥ በዙሪያሽ ያለውንም ቅጽር በከበሩ ድንጋዮች አንጻለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 54:12
Home
Bible
Plans
Videos