1
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:3
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:4
ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:4
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:9
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:9
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:12
አምላክ ሆይ፥ ሰላምን አሰፈንክልን፤ ሥራችንን ሁሉ የፈጸምክልን አንተ ነህ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:12
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:8
አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን። የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:8
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:7
አምላክ ሆይ! አንተ የጻድቃንን ጎዳና ታስተካክላለህ፤ መንገዳቸውም እንዲለሰልስ ታደርጋለህ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:7
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:5
በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል። አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:5
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 26:2
እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 26:2
Home
Bible
Plans
Videos