1
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:18
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:19
እሺ ብላችሁ ብትታዘዙኝ ምድር የምታስገኘውን በረከት ትበላላችሁ፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:19
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:17
መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:17
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:20
እምቢ ብትሉኝና ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ራሴ እግዚአብሔር ነኝ።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:20
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:16
ይልቁንስ ታጥባችሁ ንጹሕ ሁኑ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ ከፊቴ አስወግዱ፤ በደል መፈጸማችሁንም ተዉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:16
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:15
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:15
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:13
ይህን ዐይነት ከንቱ መባ ከእንግዲህ ወዲህ አታቅርቡ፤ የምታጥኑት ዕጣን በፊቴ አጸያፊ ነው፤ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት የወር መባቻችሁና ሰንበቶቻችሁ፥ መንፈሳዊ ስብሰባዎቻችሁም በኃጢአት የተበከሉ ስለ ሆኑ አልወደድሁላችሁም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:13
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:3
በሬ ባለቤቱን ያውቃል፤ አህያም የጌታውን ጋጥ ያውቃል፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ምንም አያውቅም፤ ሕዝቤም አያስተውልም።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:3
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 1:14
አዲስ ጨረቃ የምትወጣበትን የወር መባቻችሁንና በዓሎቻችሁን ጠልቻለሁ፤ እነርሱ እንደ ከባድ ሸክም ስለ ሆኑብኝ ልታገሣቸው አልችልም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 1:14
Home
Bible
Plans
Videos