1
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ጦርነትን በመልካም ተዋግቻለሁ፤ የእሽቅድድም ሩጫዬን እስከ መጨረሻው ሮጫለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ።
Compare
Explore 2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:7
2
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:2
ቃሉን ስበክ፤ ቢመችም ባይመችም በማንኛውም ጊዜ ተግተህ ሥራ፤ እያስረዳህ እየገሠጽክና እየመከርክ፥ በትዕግሥትና በማስተማር ትጋ።
Explore 2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:2
3
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:3-4
ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ። ስለዚህ እውነትን መስማት ትተው ተረትን መስማት ይወዳሉ።
Explore 2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:3-4
4
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
አንተ ግን በሁሉ ነገር ጥንቁቅ ሁን፤ መከራን በመቀበል ጽና፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህንም ሁሉ ፈጽም።
Explore 2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
5
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:8
ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።
Explore 2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:8
Home
Bible
Plans
Videos