1
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
Compare
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58
2
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:57
3
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:33
4
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:10
5
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
እንዲሁም፥ “ሞት ሆይ! ድል መንሣትህ የት ነው? ሞት ሆይ! ሰውን የምትጐዳበት ኀይል የት ነው?” ተብሎአል። የሞት መንደፊያ ኀይል ኃጢአት ነው፤ የኃጢአትም ኀይል ሕግ ነው።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:55-56
6
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ። እኛ ሁላችንም አንሞትም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን። የምንለወጠውም የመጨረሻው እምቢልታ በሚነፋበት ጊዜ እንደ ዐይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ ነው። መለከቱ ይነፋል፤ የሞቱትም ሰዎች የማይጠፉ ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፤
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51-52
7
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
ሞት የመጣው በአንዱ ሰው በአዳም ምክንያት እንደ ሆነ ከሞት መነሣትም የሚመጣው በአንዱ ሰው በክርስቶስ ምክንያት ነው። በአዳም ምክንያት ሰው ሁሉ እንደሚሞት እንዲሁም በክርስቶስ ምክንያት ሰው ሁሉ ሕይወትን ያገኛል።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:21-22
8
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይህም የሚሞተው የማይሞተውን መልበስ አለበት።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:53
9
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሁሉ በሥልጣኑ ሥር እስኪያደርግለት ድረስ ክርስቶስ መንገሥ ይገባዋል። ተሸንፎ በመጨረሻ የሚደመሰሰው ጠላት ሞት ነው።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25-26
Home
Bible
Plans
Videos