1
ምሳሌ 2:6
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።
Compare
Explore ምሳሌ 2:6
2
ምሳሌ 2:1-5
ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በልብህ ብታኖር፣ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣ እንዲሁም የመለየት ጥበብን ብትማጠን፣ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማስተዋልን ብትጣራ፣ እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፣ እንደ ተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣ በዚያን ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤ አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።
Explore ምሳሌ 2:1-5
3
ምሳሌ 2:7-8
እርሱ ለቅኖች ድልን ያከማቻል፤ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤ የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።
Explore ምሳሌ 2:7-8
4
ምሳሌ 2:21-22
ቅኖች በምድሪቱ ይቀመጣሉና፤ ነቀፋ የሌለባቸውም በእርሷ ላይ ጸንተው ይኖራሉ። ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ፤ ታማኝነት የጐደላቸውም ከእርሷ ይነቀላሉ።
Explore ምሳሌ 2:21-22
5
ምሳሌ 2:16-17
ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤ በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ታድንሃለች፤ ይህችም የልጅነት ባሏን የተወች፣ በአምላኳ ፊት የገባችውን ኪዳን ያቃለለች ናት።
Explore ምሳሌ 2:16-17
YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy
Home
Bible
Plans
Videos