1
መክብብ 9:10
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።
Compare
Explore መክብብ 9:10
2
መክብብ 9:11
ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።
Explore መክብብ 9:11
3
መክብብ 9:9
አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋራ ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።
Explore መክብብ 9:9
4
መክብብ 9:7
ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር አምላክ ደስ ብሎታልና።
Explore መክብብ 9:7
5
መክብብ 9:18
ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤ ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።
Explore መክብብ 9:18
6
መክብብ 9:17
ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣ ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።
Explore መክብብ 9:17
7
መክብብ 9:5
ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ መታሰቢያቸው ይረሳል፤ ምንም ዋጋ የላቸውም።
Explore መክብብ 9:5