1
መክብብ 5:2
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።
Compare
Explore መክብብ 5:2
2
መክብብ 5:19
አምላክ ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።
Explore መክብብ 5:19
3
መክብብ 5:10
ገንዘብን የሚወድድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው።
Explore መክብብ 5:10
4
መክብብ 5:1
ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሞኞችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።
Explore መክብብ 5:1
5
መክብብ 5:4
ለአምላክ ስእለትን በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፤ በሞኞች ደስ አይለውምና፤ ስእለትህን ፈጽም።
Explore መክብብ 5:4
6
መክብብ 5:5
ስእለት ተስሎ ካለመፈጸም፣ አለመሳል ይሻላል።
Explore መክብብ 5:5
7
መክብብ 5:12
ጥቂትም ይሁን ብዙ ቢበላ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ሰው ብልጽግና ግን እንቅልፍ ይነሣዋል።
Explore መክብብ 5:12
8
መክብብ 5:15
ሰው ከእናቱ ማሕፀን ዕራቍቱን ይወለዳል፤ እንደ መጣው እንዲሁ ይመለሳል። ከለፋበትም ነገር፣ አንድም እንኳ በእጁ ይዞ ሊሄድ አይችልም።
Explore መክብብ 5:15