ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና

የመጀመሪያው ወደ ጢሞቴዎስ የተላከ መልእክት መግቢያ
ጳውሎስ በ 63 ዓ.ም አካባቢ ይህን መልእክት ለጢሞቴዎስ እንደጻፈው ይታመናል። ይህ መልእክት ለቲቶ የተጻፈውን ጨምሮ በተከታታይ ከጻፋቸው የመጨረሻዎቹ መልእክቶች ውስጥ ይካተታል። የኤፌሶን ቤተክርስቲያንን እየመገበ ለነበረው ለወጣቱ ጢሞቴዎስ ተግባራዊ እና የመጋቢነት ጥበብን የሚያስረዳ መልእክት ጽፎለታል።
አንደኛ ጢሞቴዎስ ለቤተ ክርስቲያን አመራር ሰጪነት እና ቤተክርስትያንን እንዴት ማደራጀት እንደሚቻል መመሪያዎችን የያዘ ነው። ጢሞቴዎስ ለዓመታት ከጳውሎስ ጋር በመጓዝ በማሳለፉ ምክንያት ግንኙነታቸው እንደ አባትና ልጅ ነበር። ጳውሎስም ጢሞቴዎስን “በእምነት እውነተኛ ልጄ” ብሎ ጠርቶታል (1 ጢሞቴዎስ 1:2)። ጢሞቴዎስ በእድሜ ወጣት በመሆኑ ምክንያት የእርሱን አመራር ለመከተል በእድሜ ከፍ ከፍ ያሉ ክርስትያኖች እየተቸገሩ ስለነበር በጠባዩና በመልካም አቋሙ ጥሩ አርአያ እንዲሆን ጳውሎስ በመልእክቱ አበረታቶታል።
ስለዚህ እቅድ

በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.
More