የ 49 ሳምንት እቅድናሙና

The 49-Week Challenge

ቀን {{ቀን}} ከ341

መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ወደሚሸፍነው "49 ሳምንት እቅድ" ወደ ተባለው እቅድ በደህና መጡ። ይህንን የንባብ እቅድ ያለ ማቋረጥ ለመዝለቅ ከሚረዱ መንገዶች መካከል ይህንን እቅድ አብሮት የሚከታተል አንድ ወይም ሁለት ጓደኛ መፈለግ ነው። ማንን ወደዚህ እቅድ ይጋብዛሉ? በዚህ መተግበሪያ "እቅድ ከጓደኞች ጋር"በሚለው አማራጭ በመጠቀም በጋራ ማንበብ የምትችሉ ሲሆን ሌላው አማራጭ ደግሞ ለየብቻ በማንበብ በሳምንት አንድ ግዜ እየተገናኙ መወያየት ነው።


የዛሬውን ንባብ ለማንበብ ሲዘጋጁ እግዚአብሔርን እንዲገልፅላችሁ ጠይቁ። የሚታመን ቃልኪዳን፣ ትእዛዛትን ማክበር፣ እውነታን መቀበል፣ የሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን ማስተዋል፣ ወይም ፍፁም እረፍትን በተመለከተ ያሉ ሃሳቦች ላይ ማስታወሻ ያዙ። ማስታወሻዎቹን በመተግበሪያው ላይ መያዝ ይቻላል ወይም በማስታወሻ ደብተርም መያዝም ይቻላል። የዛሬውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ካነበቡ በኋላ አፍታ በመውሰድ እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች በማጤንና ምላሽ መስጠት ይገባል፡

ስለ እግዚአብሔር ምን ተማራችሁ፣ ስለ ራሳችሁስ ወይም ስለ ዓለም?

ዛሬ ውስጣችሁ የገባ አንድ ጥቅስ ወይም ሀሳብ አለ? ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩበት.
ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

The 49-Week Challenge

ከእግዚአብሔር ጋር ያሎትን ግንኙነት ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ማሸጋገር ይፈልጋሉ? ይህን የ 49 ሳምንት እቅድ ይከተሉ! ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እቅድ ሙሉውን መጽሐፍ ብሉይ ኪዳን እና ሐዲስ ኪዳንን በየእለቱ በማንበብ ይዘልቃል። የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በቅደም ተከተላዊ መንገድ የሚያጠኑ ሲሆን ከብሉይ ኪዳንም የተመረጡ ተቀራራቢ ክፍሎችን በማንበብ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አጠቃላይ እንዴት ወደ ኢየሱስ እንደሚጠቁም ይረዳሉ። በየሰባት ቀኑ እረፍት በመውሰድ የተማሩት ትምህርት ላይ የተለያዩ ሃሳብ እንዲሰጡ እድል ይሰጣል.

More

ይህንን እቅድ ያቀረቡልንን ላይፍ ቸርች እናመሰግናለን። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ይህንን ድህረ ገፅ ይጎብኙ፡ www.life.church