መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 12

12
የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እንደ ወረረ
(1ነገ. 14፥25-28)
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የሮ​ብ​ዓም መን​ግ​ሥት በጸ​ናች ጊዜ፥ እር​ሱም በበ​ረታ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ረሳ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ረሱ። 2ሮብ​ዓም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ዋ​ልና፤ 3ሺህ ሁለት መቶ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስድሳ ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይዞ መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከግ​ብፅ ለመ​ጣው ሕዝብ ቍጥር አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ እነ​ር​ሱም የል​ብያ ሰዎች፥ ሞጠ​ግ​ሊ​ያ​ና​ው​ያን፥#ዕብ. “ሱካ​ው​ያን” ይላል። የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሰዎች ነበሩ። 4በይ​ሁ​ዳም የነ​በ​ሩ​ትን ምሽ​ጎች ከተ​ሞች ያዙ። እስከ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረሱ። 5ነቢ​ዩም ሰማያ ወደ ሮብ​ዓ​ምና ከሱ​ስ​ቀም ሸሽ​ተው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ተሰ​በ​ሰ​ቡት ወደ ይሁዳ መሳ​ፍ​ንት መጥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ ተዋ​ች​ሁኝ፤ ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በግ​ብፅ ንጉሥ በሱ​ስ​ቀም እጅ ተው​ኋ​ችሁ።” 6የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መሳ​ፍ​ን​ትና ንጉሡ አፈሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው” አሉ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተመ​ለ​ሱና እንደ ተፀ​ፀቱ ባየ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ከተ​መ​ለሱ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም#ዕብ. “በሱ​ሳ​ቂም እጅ” የሚል ይጨ​ም​ራል። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አይ​ፈ​ስ​ስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ። 8ለእኔ መገ​ዛ​ት​ንና ለም​ድር ነገ​ሥ​ታት መገ​ዛ​ትን ያው​ቃ​ሉና አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ።
9የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ወሰደ፤ ሁሉ​ንም ወሰደ፤ ደግ​ሞም ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ዎ​ችን ወሰደ። 10ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በእ​ነ​ርሱ ፋንታ የናስ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ዎ​ችን ሠራ፤ ሮብ​ዓ​ምም የን​ጉ​ሡን ቤት ደጅ በሚ​ጠ​ብቁ በዘ​በ​ኞች አለቃ እጅ አኖ​ራ​ቸው። 11ንጉ​ሡም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በገባ ቍጥር ዘበ​ኞች መጥ​ተው ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሰ​ውም በዘ​በ​ኞች ቤት ውስጥ ያኖ​ሩ​አ​ቸው ነበር። 12በተ​ፀ​ፀ​ተም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ከእ​ርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽ​ሞም አላ​ጠ​ፋ​ውም፤ በይ​ሁዳ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና።
13ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና፤ ንጉ​ሥም ሆነ፤ ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የአ​ሞን ሴት ንዑማ ነበ​ረች። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይሻ ዘንድ ልቡን አላ​ቀ​ናም ነበ​ርና ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ።
15የሮ​ብ​ዓ​ምም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር እነሆ፥ በነ​ቢዩ ሰማ​ያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ሮብ​ዓ​ምም ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር። 16ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም አብያ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ