መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 13

13
የይ​ሁዳ ንጉሥ አብያ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር ያደ​ረ​ገው ጦር​ነት
(1ነገ. 15፥1-8)
1ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት አብያ በይ​ሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ። 2ሦስት#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ስድ​ስት” ይላል። ዓመ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገ​ባ​ዖን ሰው የኡ​ር​ኤል ልጅ ነበ​ረች። በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከ​ልም ሰልፍ ነበረ። 3አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ። 4አብ​ያም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ ባለው በሳ​ም​ሮን#ዕብ. “በጽ​ማ​ራ​ይም” ይላል። ተራራ ላይ ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ 5የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መን​ግ​ሥ​ትን ለዳ​ዊ​ትና ለል​ጆቹ በጨው#“በጨው” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ቃል ኪዳን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሰጠ በውኑ አታ​ው​ቁ​ምን? 6የዳ​ዊት ልጅ የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን ተነ​ሥቶ በጌ​ታው ላይ ዐመፀ። 7ክፉ​ዎች ሰዎ​ችና የሕግ ተላ​ላ​ፊ​ዎች ልጆ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሮብ​ዓም ሕፃን በነ​በ​ረና በልቡ ድፍ​ረት ባል​ነ​በ​ረው ጊዜ፥ ሊቋ​ቋ​መ​ውም ባል​ቻ​ለ​በት ጊዜ፥ በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ላይ በረ​ታ​በት። 8አሁ​ንም በዳ​ዊት ልጆች እጅ የሚ​ሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ልት​ቋ​ቋሙ እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ።#ዕብ. “ታስ​ባ​ላ​ችሁ” ይላል። እና​ን​ተም እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም አማ​ል​ክት አድ​ርጎ የሠ​ራ​ላ​ችሁ የወ​ርቅ እን​ቦ​ሶች ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው። 9የአ​ሮ​ንን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን አላ​ሳ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ለራ​ሳ​ችሁ ካህ​ና​ትን አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምን? አንድ ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዞ ራሱን ይቀ​ድስ ዘንድ የሚ​መጣ ሁሉ አማ​ል​ክት ላል​ሆ​ኑት ለእ​ነ​ዚያ ካህን ይሆ​ናል። 10እኛ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ው​ነ​ውም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች የአ​ሮን ልጆች ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ያገ​ለ​ግ​ሉ​ታል። 11በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል። 12እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ ካህ​ናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ይጮ​ኻሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አይ​በ​ጃ​ች​ሁ​ምና ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አቷጉ።”
13ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ጣ​ባ​ቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞ​ረ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በይ​ሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ከበ​ባ​ቸው። 14የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊ​ታ​ቸ​ውና በኋ​ላ​ቸው ነበረ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኹ፤ ካህ​ና​ቱም መለ​ከ​ቱን ነፉ። 15የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ብ​ያና በሕ​ዝቡ ፊት መታ​ቸው። 16የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከይ​ሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 17አብ​ያና ሕዝ​ቡም ታላቅ አመ​ታት መቱ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ። 18በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታም​ነው ነበ​ርና አሸ​ነፉ። 19አብ​ያም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው፤ ከእ​ር​ሱም ከተ​ሞ​ቹን ቤቴ​ል​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ይሳ​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ዔፍ​ሮ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ። 20ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከዚያ በኋላ በአ​ብያ ዘመን አል​በ​ረ​ታም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው፤ ሞተም። 21አብ​ያም ጸና፤ ዐሥራ አራት ሚስ​ቶ​ች​ንም አገባ፤ ሃያ ሁለ​ትም ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ዐሥራ ስድ​ስት ሴቶች ልጆ​ችን ወለደ። 22የአ​ብ​ያም የቀ​ረው ነገ​ርና አካ​ሄዱ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ቃሎች በነ​ቢዩ በአዶ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ